ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ የአየርላንድ አቻቸውን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

101

አዲስ አበባ  ጥር 1/2011 ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ አየርላንድ አቻቸውን ሊኦ ቫራድካርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

አየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኦ ቫራድካርን  በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ነው አዲስ አበባ የገቡት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባደረጉላቸው ግብዣ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ሲገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ማርቆስ ተክሌ አቀባበል አደርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ደግሞ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኦ ቫራድካርን ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር እንደሚወያዩም ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያ እና አየርላንድ ረዥም ዘመን ያስቆጠረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2014 የአየርላንድ ፕሬዝዳንት ሚካኤል ሄገንስ ኢትዮጵያን ጎበኝተዋል።

በወቅቱም አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የ136 ሚሊዮን ዩሮ የልማት ትብብር መፈራረሟ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም