የትግራይ ዓመታዊ የብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር ተካሄደ

72

መቀሌ ታህሳስ 30/2011 አምስት ክለቦች የተሳተፉበት የትግራይ ክልል ዓመታዊ የብስክሌት ሻምፒዮና  ውድድር ዛሬ ተካሄደ፡፡

ከመቀሌ አጎላዕና ዴስአ መስመር 90 ኪሎ ሜትር የሸፈነ የበረሃ ደርሶ መልስ ውድድር  በቡድን ደረጃ የተጓዙበት ፍጥነት በሰዓት 45 ኪሎ ሜትር ነው፡፡

ይህም ከባለፈው ዓመት ውድድር ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የክልሉ ብስክሌት ፌዴሬሽን ዳኛ አቶ ፀሐዬ አደም ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

በዚሀም በ "ቢ " ኮርስ ብስክሌት ወንዶች  ውድድር  መስፍን ሰለሞንና ነጋሲ ኪዳነማርያም አንደኛና ሁለተኛ ከጎና ሲሆኑ ገብረ መድህን ገብረእግዚአብሔር  ደግሞ ከብሩህ ተስፋ ሶሰተኛ ሆነዋል። 

በመቀሌ ከተማ ውስጥ በተካሄደው  50 ኪሎ ሜትር የሸፈነ የወንዶች " ኤ " ኮርሰ ብስክሌት ወድድር  ደግሞ ሬድዋን ሳሊህ ከትራንስ፣ አማኑኤል ብርሃኔ ከብሩህ ተስፋ  እና ኃይለ መለኮት ወልደአበዝጊ ከጉና እንደቅደም ተከተላቸው  ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ወጥተዋል፡፡  

እነዚህም በሰዓት 40 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር መጓዛቸውን  አቶ ፀሐዬ አመልክተዋል።

በክለብ የያዘት ቅደመ ተከተል ደረጃም  ጉና፣ ትራንስና ብሩህ ተስፋ  በመሆን ይመራሉ።

በሴቶች " ኤ" ኮርስ 45 ኪሎ ሜትር የሸፈነ የከተማ ውስጥ ውድድር  ትርሃስ ገብረኃይማኖት ከትራንስ አንደኛ ፣ እየሩ ተስፋሁን ከመስቦ ሁለተኛ ፣ እየሩ ሀፍቱ ከመስፍን ኢንዱስትሪያል ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

በሰዓት የተጓዙትም 35 ነጥብ 58 ኪሎ ሜትር እንደሆነ ያመለከቱት የፌደሬሽኑ ዳኛ  በክለብ  ደረጃም ትራንስ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያልና መሰቦ እንደቅደም ተከተላቸው እንደሚመሩ ገልጸዋል።

በሴቶች " ቢ"  ኮርስ  ውድድር 40 ኪሎ ሜትር በሸፈነው ውድድር  መቀሌ ሰባ እንደርታ ወክለው የቀረቡ ማህሌት መኮንን ሰርካለም ታዬ እና  ገነት መኮንን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ወጥተዋል።

በሰዓት 32 ነጥብ 69 ኪሎ ሜትር የተጓዙ ሲሆን በክለብ ደረጃም መቀሌ ሰባ እንደርታ አንደኛ ፣ ትራንስ ሁለተኛ እና መስፍን ኢንዱስትሪያል ሶስተኛ ሆነዋል፡፡

ክልሉን በመወከል በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሳተፉ የብስክሌት ስፖርተኞችን ለመምረጥ ዓላማ ያለው ይሄው ውድድር  እስከ ጥር 9/2011ዓ.ም. እንደሚቀጥልና ለአሸናፊዎችም ሽልማት እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም