በአማራ ክልል በመስኖ የሚለማውን መሬት የመለካት ሥራ እየተከናወነ ነው

1163

ባህር ዳር  ታህሳስ 30/2011 በአማራ ክልል በመስኖ የሚለማውን የመሬት ሃብት በጂ.ፒ.ኤስ ቴክኖሎጂ ታግዞ የመለካት ሥራ እየተካሄ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የልኬት ስራው በመስኖ የሚለማውን መሬት በአግባቡ ለይቶ ጥቅም ላይ ለማዋልና ከመስኖ ልማት ጋር በተያያዘ የሚቀርብ ሀሰተኛ ሪፖርትን ለማስቀረት ያግዛል ተብሏል።

እስካሁንም በ153 ወረዳዎች የተካሄደው የልኬታ ሥራ ተጠናቆ መረጃውን ወደኮምፒዩተር የማስገባት ሥራ መጀመሩ ተመልክቷል።

የቢሮው የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ ይበልጣል ወንድምነው ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ ካለፈው ሰኔ 2010 ዓ.ም ጀምሮ የልኬታ ሥራው እየተከናወነ ያለው በ182 ወረዳዎች ነው።

በመስኖ የሚለማውን የመሬት ሃብት በትክክል ለይቶ ለማወቅና ጥቅም ላይ ለማዋል የልኬታ ሥራው በሳይንሳዊ መንገድ በጂ.ፒ.ኤስ ቴክኖሎጂ ታግዞ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

“መረጃውን መሰብሰብ ያስፈለገውም በመስኖ የሚለማውን ሃብት በትክክል ለመለየትና ሃብቱን መሰረት አድርጎ የልማት ስራውን ለማከናወን ነው” ብለዋል።

ይህም በመስኖ ልማት ላይ የሚስተዋለውን ሀሰተኛና የተሳሳተ ሪፖርት ከምንጩ በማድረቅ በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ ለማቀድና የመሬት ሃብቱን በአግባቡ ለመጠቀም እንደሚያስችል አስረድተዋል።

በልኬታ ሥራውም በመስኖ የሚለማው የማሳ ስፋት፣ የአርሶ አደሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎች፣ የውሃ አማራጭ መገኛ መጠሪያ ስሞች ጭምር እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ገልጸዋል። 

እስካሁን በተከናወነው የልኬታ ስራም የ153 ወረዳዎች ሥራ ተጠናቆ የማሳ ልኬታና የካርታ ስራዎችን ወደኮምፒዩተር የማስገባት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም አቶ ይበልጣል አስረድተዋል።

“ልኬታውን እስካሁን ያልጀመሩ ድዌ፣ ሀረዋና ጃዊ ወረዳዎች እንዲሁም የጎንደርና የደሴ ከተማ አስተዳደሮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ ጀምረው ያላጠናቀቁ ናቸው” ብለዋል።

ያልጀመሩትም ሆኑ ጀምረው ያላጠናቀቁ ወረዳዎች እስከ መጪው ሚያዚያ ወር 2011 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ሙሉ በሙሉ አጠናቀው እንዲጨርሱ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ተለይቶ የተጠናቀቀው መረጃም ለውሳኔ ሰጭ አካላት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ በቀጣዩ ዓመት ሥራ ላይ ይውላል።

በባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም ቡድን መሪ አቶ አንዳርግ ይመኑ በበኩላቸው በወረዳው በመስኖ የሚለማው መሬት ተለይቶ በጂፒኤስ መሳሪያ የመለካት ሥራው መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ይህም ቀደም ሲል በመስኖ ያለማውን መሬት እንደለማ ተደርጎ ሲላክ የነበረውን ሀሰተኛ ሪፖርትና የተጋነነ የምርት ግመታን ሙሉ በሙሉ እንደሚያስቀርም አስረድተዋል።