ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የዘውዲቱ መሸሻ የህጻናት ማሳደጊያን ጎበኙ

107

አዲስ አበባ ታህሳስ 28/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የዘውዲቱ መሸሻን የህጻናትና ቤተሰብ  በጎ አድራጎትና ልማት ማህበርን ጎበኙ።

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ለበጎ አድራጎት ልማት ማህበሩ ህጻናት የገና ስጦታ አበርክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በጉብኝታቸው ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ህብረተሰቡ የገናን በዓል ሲያከብር ከተቸገሩ ወገኖቹ ጋር ሊሆን ይገባል።

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በማዕከሉ ላሉ ህጻናት የአልባሳትና የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ የገናን በዓል በማስመልከት ለህጻናቱ አበርክተዋል። 

"የዘውዲቱ መሸሻን የህጻናትና ቤተሰብ  በጎ አድራጎትና ልማት ማህበር" በ1984 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን፤ ችግረኛ ህጻናትና ቤተሰቦችን ለመደገፍ የተጀመረ ነው።

ማህበሩ በአሁኑ ወቅት 70 ህጻናትን እየደገፈ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም