በድሬዳዋ አረጋውያንን ለመደገፍ ዓላማ ያደረገ የጎዳና ሩጫ ነገ ይካሄዳል

82

ድሬዳዋ ታህሳስ 20/2011 በድሬዳዋ ከተማ በዳዊት በጎ አድራጎት ማህበር የተዘጋጀ የአስር ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ነገ ይካሄዳል ።

ከሩጫው የሚገኘው ገቢ ማህበሩ በ70 ሚሊዮን ብር ለሚያስገነባው የአረጋውያን መርጃ ማዕከል  ድጋፍ የሚውል ነው።

የማህበሩ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ዮሐንስ ለኢዜአ እንደገለፁት ከአስተዳደሩ በተገኘ 5ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል እየተገነባ ነው ።

"የማእከሉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በስድስት ወር ውስጥ ይጠናቀቃል "ያሉት ሰራ አስኪያጁ ጧሪ የሌላቸውን 200 አረጋውያን በቋሚነት በመቀበል ስራ ለመጀመርና በቀጣይም የሚቀበላቸውን ቁጥር ለመጨመር መታቀዱን  አመላክተዋል ።

ከሩጫው የሚሰበሰበው ገቢ ለግንባታው የሚውል ነው።

የድሬዳዋ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ከድር ጁሃር በሩጫው ላይ አትሌቶች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና በየደረጃው የሚገኙ የድሬዳዋ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ የሚጠበቅ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ህብረተሰቡ "ቲሸርት" በመግዛት በሩጫው ላይ በመሳተፍ ለማዕከሉ ግንባታ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ  መልዕክታቸውን  አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም