በኦሮሚያ ክልል  75 ሰዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

85
ታህሳስ 16/2011 በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ 75 ሰዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር  መዋላቸውን  የክልሉ ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ  ኮሚሽነር አቶ አበበ ከበደ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በዘጠኝ የኮሚሽኑ ቅርንጫፎች ምርመራ ሲካሂድ  ነበር ብለዋል፡፡ በኮሚሽኑ እስካሁን በተከናወነው የማጣራት ሥራ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል መዋላቸውም ተገልጿል፡፡ በዚሁ መሰረት ፡- የኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ ተቋም  ዋና ዳይሬክተርና  የተቋሙ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት፤
  • አቶ ተሾመ ለገሰ
  • አቶ ተሾመ ከበደ
  • ወይዘሮ መስከረም ደበበ
የኦሮሚያ ግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ  ዋና  ዳይሬክተርና  የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት እና በአሁኑ ወቅት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑ፤
  • አቶ መሃመድ ቃሲም
  • አቶ እንዳልካቸው በላቸው
  • አቶ ይልማ ዴሬሳ
የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር
  • አቶ አብዶ ገለቶ
የኦሮሚያ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ምክትል ሀላፊ የነበሩና  በአሁኑ ወቅት የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ
  • አቶ መንግስቱ ረጋሳ
የቀድሞ የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ ፈይሳ ረጋሳ  እና  ምክትል ከንቲባ  አቶ አብዶ ገበየሁ   እንዲሁም  የሥራ ሂደት  መሪ  አቶ ገመዳ በዳሶ፤ በጅማ ዞን የማንቾ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ፋንታ በቀለ እና ሌሎች በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ  75 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ እርምጃው ገና ጅምር መሆኑን የገለፁት አቶ አበበ የኦሮሚያ ክልል  ጸረሙስና ኮሚሽንና የክልሉ መንግስት ተጠርጣሪዎችን  ለህግ ለማቅረብ  በቀጣይም በትኩረት ይሰራል፡፡ ምንጭ-  የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም