የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሀዋሳ ገብተዋል

84
ሀዋሳ ግንቦት 17/2010 የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ  የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ለመጎብኘት ሀዋሳ ገብተዋል። ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ሃዋሳ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኩም  የአሜሪካውን ግዙፍ የጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ ፒቪኤችን ጨምሮ የህንዱን ጄፒ የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ፣  ታል አፓረልና ኦንቴክስ የተባሉ ኩባንያዎችን ይጎበኛሉ፡፡ የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ ዘመናዊ ቆሻሻ ማስወገጃ የሆነውን ዜሮ ፍሳሽ ቴክኖሎጂ ይጠቀማል። ፕሬዚዳንቱም ይህንኑ ዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገጃ ተዘዋውረው ይጎበኛሉ ተብሏል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም