ሰዎችን በመግደልና በማስገደል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

1651

ታህሳስ 14/2011 በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች አባ ቶርቤ በሚል ስም ሰላማዊ  ሰዎችን፣የመንግስት አመራሮችንና የጸጥታ አካላትን ሲገድሉና ሲያስገድሉ የነበሩ  6 ግለሰቦች  በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በተደረገ ጥብቅ ክትትል  ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተገለጸ፡፡

ግለሰቦቹ  አባቶርቤ በሚል ስም ማንነታቸውን በመደበቅ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ ሰዎችን ሲገድሉና ሲያስገድሉ  እንደነበር  ተጠቅሷል፡፡ምንጭ፡- የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ