በኢሉአባቦር 43 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ተያዙ

53
መቱ ታህሳስ 14/2011 በኢሉአባቦር ዞን ቡሬ ወረዳ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 43 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃና 44 የጥይት ካዝና መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታረቀኝ አሰፋ  እንደገለፁት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ የተያዘት  ትናንት ነው ። ከጋምቤላ ክልል በኮድ 3  -92943 ኢትዮጵያ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ በአንድ ግለሰብ አማካኝነት ወደ መሀል ሀገር በመጓጓዝ ላይ እያለ በህብረተሰቡ ተሳትፎ በቡሬ ወረዳ ሲቦ ቀበሌ በተደረገው ፍተሻ ሊያዝ ችላል ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም