በአምቦ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የእርቅ ስነስርዓት እየተካሄደ ነው

90
አምቦ ታህሳስ 9/2011 በአምቦ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ በአሁኑ ወቅት የተማሪዎች የእርቅ ስነስርዓት እየተካሄደ ይገኛል። በእርቅ ስነስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአምቦ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ታደሠ ቀነአ ተማሪዎች የራሳቸውን ደስታ በራሳቸው ማምጣት እንደሚኖርባቸው ገልጸዋል። የዛሬ ሳምንት በዩኒቨርስቲው  ይህ ሁኔታ እንዳልነበረና  ዛሬ ግን አብረው ተቀምጠው  መነጋገር በመቻላቸው  የሰላም አየር እንዲነፍስ መደላድል መፍጠሩን ተናግረዋል። "ስንሰማማና አንድ ስንሆን የማንችለው ነገር የለምና አንድ ሆነን ሰላማችንን እንጠብቅ " ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል ። ከጥል ምንም ትርፍ እንደማይኖረው ጠቅሰው የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ልዩነቶችን አቻችለው ለሌሎች  አርዓያ መሆን እንደሚጠበቅባቸውም ዶክተር ታደሠ ገልጸዋል። በአምቦ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ  የቀጠለውን የተማሪዎች የእርቅ ስነስርዓት ዝርዝር መረጃን በስፍራው የሚገኘው ሪፖርተራችን እንዳደረሰን እናቀርባለን፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም