ቻይና በማንም ጣልቃ ገብነት ሳትበገር የእድገት ጎዞዋን ትቀጥላለች- ፕሬዚዳንት ዚ ጂፒንግ  

63
ታህሳስ 9/2011 ቻይና በማንም ጣልቃ ገብነት ሳትበገር የእድገት ጎዞዋን እንደምታስቀጥል የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት ዚ ጂፒንግ ተናገሩ። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት የኮሚንስት ፓርቲው 40ኛ አመት ሲከበር ባስተላለፉት መልእክት ነው፡፡ በቀድሞው መሪ ዴንግ ዚያኦፒንግ እኤአ በ1978 ዓ.ም የተጀመረውን የኢኮኖሚ ሪፎርም ቻይናን ወደ እድገት ግስጋሴ እንድታመራ አስችሏታል ያሉት ፕሬዚዳንቱ “ይህን ለማስቀጠልም የሚያግደን አንዳችም ሃይል የለም “ብለዋል፡፡ ቻይናን ለዚህ ያበቃት የሶሻሊዝም ሪኦተ አለም መሆኑን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ በሀገሪቱ ያለው የአንድ ፓርቲ የፖለቲካ ስርዓት መቀጠል እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ኤኤፍፒ እንደገበው ዚ ጂፒንግ እንዲህ አይነት ጠንከር ያለ መልዕክት አዘል ንግግር   ያስተላለፉት አሜሪካ በቻይና ላይ የንግድና የዲፕሎማሲ ጫና ለመፍጠር የምታደርገውን  ሙከራ ተከትሎ ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ “የምናደርገው ለእኛ የሚበጀንን እንጂ በማንም ጣልቃ ገብነት የማይበጀንን ከቶውንም አናደርግም” ማለታቸውንም ዘገባው አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም