የደቡብ ክልላዊ መንግስት በቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሞት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

1503

ሀዋሳ ታህሳስ 8/2011 የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ሞት የተሰማውን ጥልቅ  ሀዘን ገለጸ፡፡

የክልሉ መንግስት ዛሬ ለኢዜአ በላከው የሀዘን መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ከኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ በፓርላማ አባልነት እንዲሁም ለ12 ዓመታት ኢትዮጵያን በርዕሰ ብሔርነት ያገለገሉ፣ ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ረጅም ዘመን በዕውቀታቸውና በሙያቸው የደከሙ ናቸው፡፡

የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ “የታማኝነትና የታታሪነት ምሳሌያችን የነበሩ ናቸው” ብሏል፡፡

የክልሉ መንግስትና ህዝብ በቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ   ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡