በተለያዩ አገራት በተካሄዱ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን ድል ቀንቷቸዋል

81
አዲስ አበባ ታህሳስ 8/2011 በተለያዩ የዓለም አገራት ቅዳሜና እሁድ በተካሄዱ የማራቶንና አገር አቋራጭ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን ውጤታማ ሆነዋል። በዚሁ መሰረት በቻይና ሸንዤን በተካሄደ የሴቶች ማራቶን ሙሉ ሰቦቃ አንደኛ ስትሆን አሹ ቃሲም እና ደሲ ደቲ ሶስተኛና አራተኛ ሆነው በመግባት አሸንፈዋል። በዚሁ የሸንዤን የወንዶች ማራቶን በቀለ ሙሉነህ፣ መላኩ አበራ፣ አሸናፊ ከተማና ኃይለሚካኤል መኮንን 2ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ እና 7ኛ ደረጃን በመያዝ አሸናፊ ሆነዋል። በቱርክ መርሲን የሴቶች ማራቶንም ቆንጂት ጥላሁንና ጫልቱ ዲዳ አንደኛና ሁለተኛ በመውጣት አሸንፈዋል። በመርሲኑ የወንዶች ማራቶን ደመቀ ካሳው አራተኛ በመሆን አጠናቋል። በህንድ በተካሄደ የ25 ኪሎ ሜትር፣ በደቡብ አፍሪካ ግማሽ ማራቶን፣ በስፔን የ7 ነጥብ 6 እና የ8 ኪሎ ሜትር ውድድሮችም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል ሲል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለኢዜአ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም