ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለይፋዊ የስራ ጉበኝት ወደ ኦስትሪያ ሄዱ

60
አዲስ አበባ  ታህሳስ 8/2011 ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለይፋዊ የስራ ጉበኝት ወደ ኦስትሪያ ቪየና አቀኑ ። ፕሬዚዳንቷ ወደ ስፍራው ያቀኑበት ዋነኛ ምክንያት ነገ በሚካሄደውና የዓለም አገራትን ትብብር ወደ ዲጂታል ዘመን ማሸጋገር ላይ በሚያተኩረው ፎረም ለመሳተፍ ነው። ፎረሙ የአፍሪካ አገራትና የአውሮፓ ህብረትን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ያለመ ሲሆን ቴክኖሎጂን በመጠቀም እድገትና ልማትን ማሳለጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሏል። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂን ከማስፋፋት አንጻር እየሰራች ያለችውን ስራ አስመልክቶ በመድረኩ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ከፎረሙ ጎን ለጎንም ከተለያዩ አገራት መሪዎችና ከቴክኖሎጂ ተቋማት ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩ ከፕሬዚዳንቷ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም