ፍሊፒናዊቷ ካትሪዮና ግራይ የዘንድሮውን የዓለም የቁንጅና ውድድር አሸነፈች

58
ታህሳስ 8/2011 የ24 ዓመቷ ፍሊፒናዊት ካትሪዮና ግራይ የዘንድሮውን የዓለም የቁንጅና ውድድር(Miss Universe) አሸናፊ ሆናለች። ይህን ተከትሎም ፊሊፒንስ የዓለም የቁንጅና ውድድርን አሸናፊነት ለአራተኛ ጊዜ ወስዳለች። የዘንድሮው የአሸናፊዎች ሽልማት በታይላንድ ዋና ከተማ ባንግኮክ ተካሂዷል። አሸናፊዋ ግራይ “ልቤ በታላቅ ኩራት ተሞላች” ስትል የአሸናፊነት ደስታዋን ገልጻለች። ግራይ በውድድሩ ማሪዋናን ህጋዊ ስለማድረግ ጉዳይ ያላትን ምልከታ እንድትናገር ተጠይቃ፥ ለህክምና ጥቅም ከሆነ ህጋዊ መሆኑን እደግፋለሁ የሚል ምላሽ ተሰጥታለች። “ሰዎች በጎ ነገርን እንዲያጎለብቱ በቻልኩት ልክ ካስተማርኩኝ፥ የተሻለች ዓለም ትኖረናለች፤ ህጻናትም ከፊታቸው ደስታ መታየት ይጀምራል” ብላለች። ፊሊፒንስ የዓለም የቁንጅና ውድድርን (Miss Universe) ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 1969፣ 1973 እና  2015 ላይ ማሸነፏ ይታወቃል። ምንጭ፦ሮይተርስ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም