የአፋር ብሄራዊ ከልላዊ መንግሥት ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ ዛሬ ይካሄዳል

90
ሰመራ ታህሳስ 7/2011 የአፋር ብሄራዊ ከልላዊ  መንግሥት ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ ዛሬ ያካሂዳል። የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ  አቶ ኢድሪስ መሐመድ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ጉባዔው ዓዋጅና ሹመቶችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ጉባዔው የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ)በቅርቡ ባደረገው ሰባተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ያደረገውን የአመራር ሽግሽግና ውሳኔዎች ተከትሎ እንደሚከናወን ገልጸዋል። በዚህም የክልሉን ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ የካቢኔ አባላትን ሹመት መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል ብለዋል። ጉባዔው በአገር ደረጃ የተጀመረውን ለውጥ ወደ ክልሉ ለማውረድ የሕዝቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት የአስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት ለመወሰን የወጣን ረቂቅ ዓዋጅ መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፋር ክልል ምክር ቤት 96 አባላት አሉት።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም