የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

1804

ታህሳስ 6/2011 የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

ኢትዮጵያን ለ12 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ያለገሉት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ትናንት ሌሊት በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ከ1994 እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ  የኢትዮጵያን ርዕሰ ብሔር ሆነው አገልግለዋል።

ታህሳስ 19 ቀን 1917 ዓ.ም አዲስ አበባ የተወለዱት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ፤ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ከፓርላማ አባልነት እስከ ፕሬዚዳንትነት አገራቸውን አገልግለዋል።

ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ አፋርኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ጣሊያንኛና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎችን የሚናገሩት አቶ ግርማ ከአንድ ዓመት በፊት በሞት ከተለዩአቸው ባለቤታቸው አምስት ልጆችን አፍርተዋል።