በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት የቀድሞው የሜቴክ የስራ ሃላፊ ሻለቃ መስፍን ስዩም በቁጥጥር ስር ዋሉ - ኢዜአ አማርኛ
በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት የቀድሞው የሜቴክ የስራ ሃላፊ ሻለቃ መስፍን ስዩም በቁጥጥር ስር ዋሉ
132
አዲስ አበባ ታህሳስ 5/2011 የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ህብረት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የቀድሞ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሻለቃ መስፍን ስዩም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሻለቃ መስፍንን ፖሊስ ዛሬ ፍርድ ቤት ይዟቸው ቀርቦ የነበረ ቢሆንም ተጠርጣሪው የተያዙበትን ምክንያት እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ በመግለጻቸው የተጠረጠሩበትን ወንጀል በመርማሪ ፖሊስ ተነግሯቸው ለሰኞ ታህሳስ 8 ቀን 2011 እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፖሊስ እንደገለጸው ሻለቃ መስፍን በ7 ሚሊዮን 952 ሺህ 767 ብር የመንግስት ሃብት እንዲባክን በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረዋል። ''በተጨማሪም በመጣራት ላይ ያለ 481 ሺህ ብር በላይ ሃብት እንዲባክን አድርገዋል'' ተብሏል።