የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት ቤቶች ያደረገው የኮምፒውተር ድጋፍ ለብሔራዊ ፈተና ዝግጅት እያገዛቸው መሆኑን ተማሪዎች ገለጹ

91
አዲስ አበባ ታህሳስ 5/2011 የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለ19 ትምህርት ቤቶች ያደረገው የ500 ኮምፒውተር ድጋፍ ለብሔራዊ ፈተና ዝግጅት እያገዛቸው መሆኑን ተማሪዎች ገለጹ። የኮምፒውተር ድጋፉ ተማሪዎች የተለያዩ አጋዥ መጽሃፍትን በቀላሉ ለማግኘት እንዳስቻላቸው ተነግሯል። የኢዜአ ሪፖርተር ድጋፍ ከተደረገላቸው ትምህርት ቤቶች ውስጥ በጂንካ ከተማ የሚገኙትን የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ መሰናዶ ትምህርት ቤትና የጂንካ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል። ትምህርት ቤቶቹ  ከአሁን በፊት የኮምፒውተር እጥረት እንደነበረባቸው ተማሪዎቹ ተናግረዋል። የጂንካ ሚሊኒየም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 10ኛ ክፍል ተማሪ ስዩም ገዛኸኝ በሰጠው አስተያየት"አምና ብዙ ኮምፒውተር አልነበረም የነበሩትም ኮመፒውተሮች ጤናማ ኮምፒውተሮች አልነበሩም አሁን ብዙ ኮምፒውተር በመኖሩ  ተጠቅመናል።˝ ሁለቱ ትምህርት ቤቶች እያንዳንዳቸው 50 ኮምፒውተር ድጋፍ ከተደረገላቸው በኋላ ተማሪዎቹ የሚፈልጉትን መረጃ በቀላሉ ማግኘት መቻላቸውንና ለፈተና ዝግጅት ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። የጂንካ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ መሰናዶ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሜላት ብርሃኑ ተማሪ ሊዲያ ታደገ በአስተያየቷ ወደ ሃምሳ ኮምፒውተር ወደ ትምህርት ቤቱ መጥቷልና አሁን ባለሁበት ሁኔታ የ11ኛ ክፍልን በተወሰነ መልኩ ለማገባደድ እየሞከርኩ ነው እና ከአስተማሪዎች ቀደም እያልኩ የ12ኛ ክፍል ትምህርትንም እያነበብኩ ነው" ዩኒቨርሲቲው ካደረገላቸው የኮምፒውተር ድጋፍ በተጨማሪ ለመምህራን የኮምፒውተር አጠቃቀም ስልጠና ድጋፍ እንዳደረገላቸው የሚናገሩት ደግሞ የትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን ናቸው። የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር ገብሬ ይንቲሶ በበኩላቸው ድጋፉን ያደረጉት የአካባቢውን ባለሃብቶችና የተራድኦ ድርጅቶችን በማስተባበር ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ይህን መሰሉን ማህበራዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።      ዩኒቨርስቲው ስራ ከጀመረ ገና ሁለተኛ አመቱን የያዘ ሲሆን በጀመረው የማህበረሰብ አገልግሎት ከኮምፒውተሮቹ በተጨማሪ በርካታ የመማሪያ ወንደርና ጠረጴዛዎችን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶችንም በስጦታ መስጠቱን ተናግረዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም