ቱርክ ውስጥ በፈጣን ባቡር ላይ በደረሰ አደጋ 9 ሰዎች ሲሞቱ 47 ተጎድተዋል

53
ታህሳስ 4/2011 በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ ፈጣን ባቡር በመተላለፊያ መስመር ላይ ከባቡር ሃዲድ ፈታሽ ሎኮሞቲቭ ጋር ተጋጭቶ 9 ሰዎች ሲሞቱ 47 መጎዳታቸውን የትራንስፖርትና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ካሂት ቱርሃን ተናግረዋል። ባቡሩ ከአንካራ ወደ ማዕከላዊ ቱርክ ኮንያ እየሄደ ካጋጠመው አደጋ በኋላ መገልበጡን የአንካራ አስተዳደር ገልጿል። የነፍስ ማዳን ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን ተጎጂዎቹ ወደ ህክምና ማዕከላት እየተወሰዱ ነው። የአደጋውን ዝርዝር ሁኔታ እየተመረመረ ነው ተብሏል።ምንጭ፦አናዶሉ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም