አካዳሚው ለስፖርት ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ነው

61
አዲስ አበባ ታህሳስ 2/2011 የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለስፖርት ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ነው። በስልጠናው ከ150 በላይ የተለያዩ አይነት የስፖርት ባለሙያዎችና አሰልጣኞች ተሳታፊዎች ሆነዋል። የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ አንበሳው እንየው እንደገለፁት በስልጠናው የስፖርት ማእከላት፣ በእግር ኳስ፣ አትሌቲክስና ሌሎች ፌዴሬሽን አሰልጣኞች እንዲሁም የክልል ስፖርት ባለሙያዎች ተሳታፊ ናቸው። የስልጠናው ትኩረትም በአሰለጣጠን ሂደት ስፖርተኞች የሚያሳዩትን ስፖርታዊ ለውጥ ወይም መሻሻል መመዛዘን የሚያስችል ግንዛቤ መፍጠር መሆኑን ጠቁመዋል። በመሆኑም አሰልጣኞች በቅድመ ውድድርና ከውድድር በኋላ የስፖርተኞችን የብቃት ደረጃ በቀላሉ እንዲያውቁ ያስችላቸዋል ብለዋል። የአሰለጣጠን ሂደትን ለማሻሻል እንዲሁም ሙያዊ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማድረግም እገዛ ይኖረዋል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ታዳጊ ስፖርተኞችን በማሰልጠን ለክለቦችና ብሄራዊ ቡድን ግብአት በማድረግ እንዲሁም በስፖርቱ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ስራዎችን ያካሂዳል። በአካዳሚው ባለሙያዎች በዛሬው እለት መሰጠት የተጀመረ ስልጠና በነገው እለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም