በአምስተኛው ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መከላከያን አሸነፈ

75
አዲስ አበባ ታህሳስ 1/2011 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መከላከያን 1 ለ 0 አሸነፈ። ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በ11:00 ሰዓት በተደረገው የፕሪሚየር ሊጉ አምስተኛ ሳምንት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መከላከያን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል። ለወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የማሸነፊያ ጎሉን አፈወርቅ ሃይሉ አስቆጥሯል። በዚህም መሰረት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 6ኛ ማሻሻል የቻለ ሲሆን በአንጻሩ መከላከያ ደግሞ በነበረበት 11ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። ፕሪሚየር ሊጉን ሀዋሳ ከተማ 10 ነጥብ በመያዝ አንደኛ ሆኖ እየመራ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና በእኩል 8 ጎሎች በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ስሁል ሽረ፣ አዳማ ከተማ እና ደደቢት ከ14ኛ እስከ 16ኛ ደረጃ ላይ  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም