በኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ አዲስ አበባ ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ 2ኛ ከፍ አደረገ

152
አዲስ አበባ ታህሳስ 1/2011 በኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ አዲስ አበባ ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ 2ኛ  ከፍ አደረገ። በኢትዮጵያ አንደኛ ዲቪዚዮን የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተካሄዱት የ3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች አዳማ ከተማ፤ አዲስ አበባ ከተማን ሁለት ለዜሮ አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ በዚሁ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ሰርክአዲስ ጉታ ባስቆጠረቻቸው ሁለት ግቦች ነው አደማ ከተማ አሸናፊ የሆነው። በጨዋታው አዳማ ከተማ ብዙ የግብ ዕድሎችን ባለመጠቀሙ ብዙ ጎሎችን አባክኗል። በአንጻሩ አዲስ አበባ ከተማ ጎል ማስቆጠር የሚችልበትን አድል መፍጠር ተስኖት ነው ጨወታው የተጠናቀቀው። በውጤቱ መሰረትም አዳማ ከተማ ነጥቡን ወደሰባት ከፍ በማድርግ ይዞት ከነበረው የ6ኛነት ደረጃ ወደ 2ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል። በአንጻሩ አዲስ አበባ ከተማ ከነበረበት 2ኛ ደረጃ ወደ አምስተኛ ደረጃ ወርዷል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሜየር ሊግን በዘጠኝ ነጥብ ሲመራ አደማ ከተማ በሰባት ነጥቦች እየተከተለ ነው። መከላከያ እና ጌዲዮ ዲላ አዲስ አበባ ከተማ በተመሳሳይ ስድስት ነጠብ ይዘው በግብ ክፍያ ተበላልጠው ከሶስት እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።                        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም