ኢትዮጵያዊያን መከፋፈልን በመተው በአንድ ላይ ወደፊት መጓዝ ይገባናል - የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

56
አዲስ አበባ ህዳር 29/2011 ኢትዮጵያዊያን የሚጠቅማቸው መከፋፈልና መለያየት ሳይሆን በአንድ ላይ ወደፊት መጓዝ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ተናገሩ። እነሆ ዛሬ ለ13ኛ ጊዜ የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የበርካታ ታላላቅ አለም አቀፋዊ ድርጅቶች መናኸሪያ በሆነችው በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል። የኢትዮጵያ ህዝቦች እስካሁን ድረስ በቀደመ ታሪካቸው አያሌ ፈተናዎችን ያለፉ ቢሆንም በመቻቻል ስሜት በፍቅርና በአንድነት አብረው ቆይተዋል። በመሆኑም የሚጠቅማቸው በጥቃቅን ችግሮች ምክንያት የሚከሰቱ ግጭቶችን በመተው አንድ መሆን ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ ገልፀዋል። የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የቲያትር ጥበባት የሁለተኛ አመት ተማሪ ወጣት አሸናፊ ካሳዬ እንዳለው "ሁሉም የራሱን ልብስ መለያ ነው ለብሶ የሚመጣው እዚህ ጋር ግን እኛ ይሄ ቀን አንድ ኢትዮጵያ መሆን አለበት ለምን ቢባል እስከዛሬ እነ አጼ ቴዎድሮስ፣ ሚኒሊክ ሃይለስላሴ ለአንድ ኢትዮጵያ ነው ሲዋጉ የኖሩት በዚህ ሰአት ግን እንደስጋ ተከፋፍለናል ከየትኛውም ክልል መጥቶ አንድ ላይ ይሰበሰባል እዚህ ጋር ተሰብስበን ለኢትዮጵያዊነታችን ኢትዮጵያ እኛ ስንኖር ነው የምትኖረው መከፋፈል የለብንም።" "ብሄር ብሄረሰቦች በቃ አንድነታቸውንና ባህላቸውን የሚያስተዋውቁበት ተጣልተው የሚታረቁበት ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያዊነታቸው አንድ ቦታ ላይ መዲናችን ላይ ነው የሚከበረው እና በዚህ ሰዓት ፍቅርን ባህላቸውን ነው መተዋወቅ ያለባቸው።ወጣት ዮሃንስ አፈወርቅ የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት የሲቪል ኢንጂነሪንግ ተማሪ የዘንድሮው የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የተከበረው ''በብዝሃነት የደመቀ ኢትዮጵያዊ አንድነት' ' በሚል መሪ ሀሳብ ነው። በዓሉ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በራሳቸውና በተወካዮቻቸው አማካኝነት እርስ በእርስ የሚተዋወቁበት፣ ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት፣ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩበት፣ የጋራ እምነቶቻቸውንና ተስፋቸውን የሚጋሩበት ቀን ተደርጎም ይወሰዳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም