ህዳር 29 የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በልዩ ልዩ መርሃግብሮች በመከበር ላይ ነው

259
አዲስ አበባ ህዳር 29/2011  የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች በመከበር ላይ ነው። በአዲስ አበባ አስተናጋጅነት የሚከበረው የዘንድሮው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የኢትዮጵያዊነት በዓል እያንዳንዱ ብሔር የየራሱን ባህልና ወግ የሚያጎላበት ብቻ ሳይሆን አንዱ የሌላውን በማጌጥ ከልዩነት ይልቅ በአንድነት መተሳሰር የሚጎላብት ሁነት ነው። ከሰሞኑ በልዩ ልዩ ፓናል ውይይቶች፣ አውደ ርዕይዮች፣ የሙዚቃ ድግሶች፣ ሲምፖዚየሞች፣ ባዛሮች፣ የጎዳና ላይ ትርኢቶችና ለሰላም ቡና ጠጡ ፕሮግራሞች ደምቃ የሰነበተችው መዲናዋ፤ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የብሔሮች ተወካዮች፣ ተማሪዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት የማጠቃለያውን ፕሮግራም ይካሄዳል። በተያዘው መርሃ ግብርም የመከላከያና ፖሊስ ማርሽ ባንዶች፣ የማስ ስፖርት ትርኢቶች፣ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች የባህል ትርኢቶች ደምቀው የሚታዩበት ይሆናሉ። በተጨማሪም  የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የመዲናዋ ምክትል ከንቲባ፣ የምክር ቤቶች አፈጉባዔዎችና የጎረቤት አገራት መሪዎች መልዕክቶች እንዲሁም የሄሊኮፕተር  እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት  እና የሽልማት ስነ ስርዓቶች  በበዓሉ ላይ የሚከናወኑ ሁነቶች ወስጥ ናቸው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም