በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው

528

አዲስ አበባ ህዳር 27/2011 በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየመከሩ ነው።

በምክክሩ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች በተጨማሪ አባ ገዳዎች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አክቲቪስቶችና የፖለቲካ ምሁራን አየተሳተፉ ነው።

በመድረኩ መክፈቻ የአገሪቱንና የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ የሚያመላክቱ የውይይት መነሻ ጽሁፎች ቀርበዋል።

በጽሁፉም በኢትዮጵያ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ተዳሰዋል።

በቀጣይም ጽሁፉን መነሻ በማድረግም ፓርቲዎች ውይይት አድርገው የጋራ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ውይይቱ “ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገው ሽግግርና የኦሮሚያ ክልል ተጨባጭ ሁኔታ” በሚል ርዕስ ነው እየተካሄደ ያለው።

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ 14 የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ተገኝተዋል።