በነ ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለመፍቀድ ወይም ላለመፍቀድ ለአዳር ተቀጠረ

77
አዲስ አበባ ህዳር 26/2011 ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውና ወንድማቸው ኢሳያስ ዳኘው ላይ ለፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ለመፍቀድ ወይም ዋስትና ለመፍቀድ ፍርድ ቤቱ ለአዳር ቀጠረ። ፖሊስ ሜጀር ጀኔራል ክንፈ በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ በመሆናቸው ምርመራ ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውና ወንድማቸው ኢሳያስ ዳኘው ላይ ፖሊስ ባቀረበው የጽሁፍ ማስረጃ ላይ ጊዜ በመውሰድ ምላሽ ለመስጠት የተጠርጣሪ ጠበቆች ባለፈው ሰኞ እስከ ረቡዕ ጊዜ እንዲሰጣቸው በጠየቁት መሰረት ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው ጉዳያቸው ለአዳር ተቀጥሯል። ዛሬ በነበረው ችሎት የሜጀር ጀኔራል ክንፈ ጠበቆች ''ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊፈቀድ አይገባም'' ብለው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል። ወንድማቸው አቶ ኢሳያስ ክንፈም ''የተጠረጠርኩበት ወንጀል አግባብ አይደለም'' ብለዋል። ''ከወንድማቸው ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ጋር ተጣምረው መከሰስ የለባቸውም'' ሲሉ ጠበቆቻቸው ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል። የግራ ቀኝ ክርክሩን ያደመጠው ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ለመፍቀድ ወይም ዋስትና ለመፍቀድ ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም