በዝምባቡየ የኢኮኖሚ ቀውስ ኤች አይ ቪን ለመከላከል አዳጋች እያደረገ ነው

1660

ህዳር 23/2011 በዝምባቡየ የኢኮኖሚ ቀውስ ኤች አይ ቪን ለመከላከል አዳጋች እያደረገው ነው ተባለ፡፡

መረጃው እንዳሚያመለከተው በሀገሪቱ በተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ የኤች አይ ቪ ወረርሽኝን ለመዋጋት የመድሃኒቶች ክምችት እጥረት እየተከሰተ ነው፡፡

በዚህም መድሃኒት ቢገኝም የሀገሪቱ ገንዘብ  በየእለቱ ዋጋ እያጣ በመሄዱ እና አብዛኞቹ አቅራቢዎች የሚቀበሉት በዶላር ብቻ በመሆኑ ፋርማሲዎችና ሆስፒታሎች መድሃኒቱን በቋሚነት ለማከማቸት እንዳልቻሉ ነው የተገለጸው፡፡

ይህም ቫይረሱ በደማቸው የሚገኙት ህሙማን በቋሚነት መድሃኒት ለማገኘት አዳጋች እየሆነ መምጣቱን ዶክተሮቹ ስጋታቸውን ገልጸው ይህም ደግሞ መድሃኒት እንዲቆራረጥ በማድረግ ቫይረሱ መድሃኒትን የመላመድ አዝማሚያ ይዳርጋል ብለዋል፡፡

በዚምባብዬ የሚገኙ ዶክተሮቹም እንዳስረዱት ህመምተኞች መድሃኒቱን ካላገኙ/መውሰድ ካቆሙ በጣም ከባድ ከመሆኑም ባለፈ መድሃኒት ከተላመደ ድጋሚ ለማከም  በጣም ከባድ እንደሚያደርገው አልጀዚራ ዘግቦታል፡፡