ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከ100 ተፅእኖ ፈጣሪ አፍሪካውያን ውስጥ ተካተዋል

1155

ህዳር 22/2011 ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድና ሌሎች ስድስት ኢትዮጵያውያን በኒው አፍሪካን መጽሄት “100 ተፅእኖ ፈጣሪ አፍሪካውያን” ውስጥ ተካተዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የካቢኔ አወቃቀርንና በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ሹመትንም  የፆታ እኩልነትን በማረጋገጥ  ረገድ  ያለውን በጎ ሚና መፅሄቱ በዘገባው ለአብነት አንስቷል፡፡

እንደ መፅሄቱ ገለፃ ተፅእኖ ፈጣሪዎቹ የተመረጡት በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈረንጆች 2018 አፍሪካውያን ላይ ባሳረፉት በጎ ተፅእኖና በቀጣዩ አመትም በሚኖራቸው ተጠባቂ በጎ ሚና ነው፡፡

በመፅሄቱ የተመረጡ ተፅእኖ ፈጣሪዎች በፆታ ስብጥር  እኩል በኩል ሴትና ወንድ ናቸው፡፡