ትልቁ ጆርጅ ቡሽ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

1072

አዲስ አበባ ህዳር 22/2011 የአሜሪካው አርባ አንደኛ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ትላንት ማምሻውን በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የቀድሞ የአሜሪካን ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ በሚኖባት የቴክሷስ ግዛት በሁስቶን ከተማ ህይወታቸው ማለፉን ቃል አቀባያቸው ተናግሯል።

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1989 እስከ 1993 የዴሞክራቲክ እጩ ተወዳዳሪውን ሚካኤል ዱካኪስ አሸንፈው አገራቸውን በፕሬዚዳንትነት አገልገለዋል።

የቀዝቃዘው ጦርነት እንዲቋጭና አሜሪካ ከሩስያ ጋር ያላትን ግንኙነት ሰላማዊ ለማድረግ ፕሬዚዳንቱ አበርክቷቸው ከፍተኛ ነበር ይባላል።

በርዕዮተ-ዓለም ልዩነት ሳቢያ የተገነባው የበርሊን ግንብ ከፈረሰ በኋላ ጀርመን ዳግም አንድ እንድትሆንም ጆርጅ ቡሽ ያላሰለሰ ጥረት ማድረጋቸውም ተጠቁሟል።

ኢራቅ ኩዌትን መውረሯን ተከትሎም አሜሪካ አገራትን በማስተባበር የኢራቅ መንግሥት ከድርጊቱ እንዲቆጠብም ፕሬዚዳንቱ ጉልህ ድርሻ ተጫውተዋል።

አሜሪካ ከጥምር የአገራት ቡድኑ ጋር ባደረገችውም ውጊያ ኢራን ላይ ድል ከተቀዳጀች በኋላ አዲስ የዓለም አሰላለፍ ለዓለም አስተዋውቀውም  ነበር።

በአገራቸው የውስጥ ጉዳይም የአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነትን በተመለከተና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያወጧቸው ሕጎች ከሰሯቸው ሥራዎች ተጠቃሽ ናቸው።

ከዛ አስቀድሞ በፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬጌን እ.አ.አ 1981 እስከ1989 ደግሞ ለሁለት ጊዜ ያክል ምክትል ፕሬዚዳንትም ሆነው አገልግለዋል።

እ.አ.አ ከ1976 እስከ 1977 ደግሞ የማዕከላዊ ስለላ ተቋም ዳይሬክተር ፣ በቻይና የአሜሪካ ጽህፈት ቤት ሁለተኛው ዋና ጸኃፊ በመሆንም እ.አ.አ 1974 ድረስ 1975 ሠረተዋል።

እ.ኤ.አ ከ1973 እስከ 1974 ደግሞ 49ኛውም የሪፐብሊካን ብሔራዊ ኮሚቴ ሊቀ-መንበርም ሆነው ያገለገሉት ጆርጅ ቡሽ በመንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ሆነውም እ.ኤ.አ ከ1971 እስከ 73 አገልግለዋል።

እ.ኤ.አ ከ1967 አስከ 1971 ድረስ ደግሞ የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አባልም ነበሩ።

ጎን ለጎንም ፕሬዚዳንቱ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የጦር ተዋጊ ጀት አብራሪ፣ በቴክሳስ በነዳጅ ሥራ የተሰማሩ ግለሰብም ነበሩ ተብሏል።

በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያ ፕሬዚዳንትም ናቸው ልጃቸው “ጆርች ቡሽ ትንሹ” የራሳቸውን ፈለግ በመከትል ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾመላቸው።

ጆርጅ ቡሽ በማሳቹሴትስ ግዛት በሚልቶን ከተማ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1924 ሓምሌ 12 ነበር የተወለዱት።

የእድሜ ባለፀጋው ጆርጅ ቡሽ የነርቭ ሰርዓትን በማዛባት አካላዊ አንቅስቃሴን በሚገታው ፓርኪንሰን የተሰኘ ህመም ሲሰቃዩ እንደነበር ሲኤን ኤንንና ቢቢሲን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ፕሬዚዳንቱ የስድስት ልጆች አባት ነበሩ።