የምርት ገበያው የአባልነት መቀመጫ ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ ተሸጠ

50
አዲስ አበባ ህዳር 21/2011 የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የአባልነት መቀመጫ በ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ተሸጠ። ምርት ገበያው የአባልነት መቀመጫዎቻቸው እንዲሸጡላቸው ለሚጠይቁ አባላት በየሩብ ዓመቱ ጨረታ በማውጣት ይሸጣል። በዚህም መሰረት ሶስት የመደበኛ አባልነት መቀመጫዎችን ለመሸጥ ባካሄደው ጨረታ እስከ 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የጨረታ ዋጋ ላቀረቡ ተጫራቾች የአባልነት መቀመጫዎች ሸጧል። ይህ የመገበያያ መቀመጫ ተገበያይና አገናኝ አባል በመባል የሚታወቁ ሁለት አይነት የአባልነት መደቦች እንዳሉት ለኢዜአ ገልጿል። ተገበያይ አባል የሚገበያየው በራሱ ስም ሲሆን አገናኝ አባል ደግሞ በራሱ ወይም በደንበኞች ስም መገበያየት የሚያስችል የአባልነት አይነት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ 347 አባላት አሉት።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም