ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተለያዩ ሹመት ሰጡ

97
ህዳር 18/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ሹመት የተሰጧቸው  የስራ ሀላፊዎች፦ 1.ዶ/ር አምባቸው መኮንን - በጠቅላይ ሚንስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚንስትር 2.አቶ ገ/እግዚአብሔር አርአያ- በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ 3.አቶ ጫኔ ሽመካ- በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ 4.አቶ ጫላ ለሚ- በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ 5.አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ- በጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር ዴኤታ 6. ብርጋዴል ጄኔራል አህመድ ሀምዛ -የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር 7.አቶ ሞቱማ መቃሳ- የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር ዴኤታ 8.አቶ ከበደ ይማም-  የአካባቢ ጥበቃ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር 9.አቶ አዘዘው ጫኔ- የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር 10.አቶ አወል አብዲ- የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር 11.አቶ ሙሉጌታ በየነ- የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር/ 12.ዶ/ር ፅጌረዳ ክፍሌ -(የብሔራዊ ኤች. አይ. ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር 13.ወ/ሮ ያምሮት አንዱዓለም- የአርማወር ሐሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር 14.ዶ/ር ሚዛን ኪሮስ- የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር 15.አቶ ሀሚድ ከኒሶ- የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር 16.አቶ ከበደ ጫኔ- የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር 17.ወ/ሮ ምስራቅ ማሞ - የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል፡፡ ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም