በአሶሳ ዩኒቨርስቲ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር ዋለ

135
አሶሳ ህዳር 18/2011 በአሶሳ ዩኒቨርስቲ ትናንት ማምሻውን የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። የአሶሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አኑር ሙስጠፋ  ለኢዜአ እንደገለፁት በዩኒቨርስቲው ወንዶች ማደሪያ ተነስቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ መንሰኤ ከኤሌክትሪክ መነካካት ጋር ተያይዞ ነው ብለዋል ። "የእሳት አደጋ ሰራተኞች በአፋጣኝ ደርሰው ቃጠሎውን በቁጥጥር ሊያውሉት ችለዋል "ብለዋል ። "በቃጠሎው የተጎዳ ሰው የለም " ያሉት ኮማንደሩ አደጋው ያደረሰው የጉዳት መጠን እየተጠራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም