ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው

65
ህዳር 18/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በቀጣዩ ምርጫና በወቅታዊ የአገሪቷ ጉዳይ ዙሪያ እየተወያዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ  አሁን ላይ በሀገሪቱ ስለተጀመረው ዘርፈ ብዙ ለውጥና በሚቀጥለው ዓመት የሚደረገውን ሀገራዊ ምርጫ ነፃና ፍትሃዊ ለማድረግ ሊወሰዱ በሚገባቸው አስፈላጊ እርምጃዎች ዙሪያ ነው ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር የሚወያዩት። ውይይቱ የሚካሄደው በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ ሲሆን በርካታ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎችም ተገኝተዋል። በውይይቱ ላይ በሀገር ውስጥ የተመዘገቡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና በመንግስት ጥሪ ተደርጎላቸው ከውጭ ሀገር የተመለሱ ፓርቲዎች እየተሳተፉ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገሪቷ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ዘርፈ ብዙ ለውጦች መካከል የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት ቀዳሚው መሆኑን ደጋግመው ሲገልጹ እንደነበር ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም