ከሜቴክ ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት እነ ፍጹም የሺጥላ ፍርድ ቤት ቀረቡ

71
አዲስ አበባ ህዳር 17/2011 ጋዜጠኛ ፍጹም የሺጥላን ጨምሮ ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ተጠርጣሪዎቹ አንደኛ ትዕግስት ታደሰ፣ ሁለተኛ ፍጹም የሺጥላ እና ሶስተኛ ቸርነት ዳና ናቸው። አንደኛ ተጠርጣሪ ሃብት በማካበት፣ሁለተኛ ተጠርጣሪ በማስታወቂያ ስፖንሰር ስም ጥቅም በማጋበስ፣ የሜቴክ አባል ሳይሆኑ ለ30 ቀናት አሜሪካ በመሄድና በዚህም ከ11 ሺህ ዶላር በላይ እንደተከፈላቸው ተገልጿል። ሶስተኛ ተጠርጣሪም የቻይና ኩባንያን ወክለው በመደለል ሜቴክ 1 ሺህ 480 የእርሻ ትራክተር ከዕቅድ ውጪ እንዲገዛ በማድረግ 42 ሚሊዮን ዶላር እንዲባክን አድርገዋል በሚል ተጠርጥረዋል። ጠበቆች ዋስትና ሲጠይቁ፤መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀናትን የጠየቀ ሲሆን ችሎቱም የ10 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል።                                                              
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም