በኮረም ከተማ ሀገር አቀፍ የአትሌቲክስ መንደር ሊገነባ ነው

89
መቀሌ ህዳር 5/2011 በትግራይ ደቡባዊ ዞን  ኮረም ከተማ  ሀገር አቀፍ የአትለቲክስ መንደር ለመገንባት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነሰርዓት ተካሄደ፡፡ በዚሁ ስነስርዓት ወቅት  የኮረም ከተማ አስተዳደር  ከንቲባ ዳርጌ መረሳ እንዳሉት ከ22 ሄክታር በሚበልጥ ስፍራ የሚገነባው የአትሌቲክስ መንደር ከ40 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ  ነው። እስካሁን ከትግራይ መለሶ ማቋቋም ተቋም የ22 ሚሊዮን ብር መስጠቱን አመልክተው ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ባለሃብቶች ደግሞ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ቃል መገባቱን  አስታውቀዋል። የአትሌቲክስ መንደሩ በተሰጠውና ግንባታ ቃል በተገባው የትራክና የአጥር ግንባታ እንደሚካሄድ ፣  የስፖርት ማሰልጠኛና ሌሎችም ተጓዳኝ ስራዎች እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ "የሀገር አቀፍ አትሌቲክስ መንደር ግንባታው በሰባት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ አስተዳደሩ  ጠንክሮ ይሰራል "ብሏል። መሰረተ ድንጋይ ያኖሩት የትግራይ መልሶ ማቋቋም ተቋም ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ በበኩላቸው ለመንደሩ ግንባታ የሰጡት የገንዘብ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ እንዳልሆነ ገልፀዋል። "የኮረም ከተማ ህዝብና አስተዳደሩ  በጠየቁን መሰረት የትእምት ቦርድ ተነጋግሮ በመሰን ወደ 22 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ  ሰጥቷል፤  ድጋፍ ትራኩን እስከሚጠናቀቅ ድረስ የትእምት ቦርድና ተቋሙ ከጎናቸው በመሆን  እንደሚንቀሳቀሱ በዚህ አጋጣሚ ላረጋግጥላችሁ  እፈልጋለሁ" ብለዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴረሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም  በመሰረተ ድንጋይ ማኖር ስነ ስርዓት ተገኝቶ እንደተናገረው የአትሌቲክስ መንደር ግንባታው ለትግራይ ብቻ ሳይሆን  ሀገሪቱን  ወክሎው የሚወዳደሩ አትሌቶችን ለማፍራት ያግዛል፡፡ ለግንባታው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጿል፡፡ ስፖርት አምራች ዜጋ ለማፍራት ከሚያስችሉ ስራዎች አንዱ በመሆኑ ሁሉም አካባቢዎች ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩም መልዕክቱን አስተለልፋል፡፡ ከኮረም ከተማ ነዋሪዎች መካከል ሊቀ ትጉሃን ሞላ በየነ በሰጡት አስተያየት " በመንግስታችን እየደረገ ያለው የልማት አካል የሆነ የአትሌቲክስ መንደር ለመገንባት ዝግጅት መደረጉ ደስተኞች ነን "ብሏል። በኮረም ሀገር አቀፍ አትሌቲክስ መንደር የመሰረተ ድንጋይ የማኖር ስነ ስርዓት ወቅት  የከተማው ነዋሪ ህዝብ፣  የክልል፣የዞንና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም