በሕገ ወጥ የደን ውጤቶች ዝውውር የተሰማራው ግለሰብ ሦስት ዓመት ከሰባት ወራት እሥራት ተቀጣ

80
መቱ ህዳር 15/2011 በኢሉአባቦር ዞን የመቱ ወረዳ ፍርድ ቤት ሕገ ወጥ የደን ውጤቶችን ሲያዘዋውር የተገኘውን ግለሰብ የሶስት ዓመት ከሰባት ወራት እሥራት ፈረደበት፡፡ የወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አዲሱ አብዲሳ ለኢዜአ እንደገለጹት በወንጀለኛው ላይ የቅጣቱ የተላለፈው 45 ሜትር ኪዩብ የደን ውጤቶችን በሕገወጥ መልኩ ጭኖ ሲያጓጉዝ በመገኘቱ ነው፡፡ መሐመድ አልዪ የተባለው ግለሰብ   የደን ውጤቶቹን ጥቅምት 7 ቀን 2011 ደኑን ዲዱ ወረዳ በጭነት ተሸከርካሪ  አድርጎ ወደ አዲስ አበባ በማጓጓዝ ወንጀሉን መፈጸሙ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል። በመቱ ከተማ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የደን ውጤቶች ከሚመለከተው አካል እውቅናም ይሁን ፈቃድ እንዳልተሰጣቸው ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። ድርጊቱን የወረዳው ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው የሰነድና የሰው ማስረጃ  መረጋገጡንም አመልክተዋል። የደን ውጤቶቹ ተሸጠው ለመንግሥት ገቢ እንዲሆኑ መወሰኑን አቶ አዲሱ ገልጸዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም