ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ጋር ሊወያዩ ነው

1894

ህዳር 14/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ህዳር 18/2011 ዓ.ም ከተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ጋር ሊወያዩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ጋር የሚያደረርጉት ውይይት በሀገሪቱ ስለተጀመረው የዴሞክራታይዜሽን ጉዞ እና የቀጣይ ዓመት አገራዊ ምርጫ ነጻ እና ፍትሀዊ ለማድረግ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው አስፈላጊ የሪፎርም ስራዎች ዙሪያ  እንደሚወያየዩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዳራሽ በሚካሄደው ስብሰባም የሁሉም ፖለቲካ ፓርቲ ሊቀመናብርት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ውይይቱም በሀገር ውስጥ የተመዘገቡ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን እና ጥሪ ተደርጎላቸው ከውጭ የመጡትን ፓርቲዎች ያካትታል ነው የተባለው፡፡