ጓቲማላዊው የቀድሞ ወታደር በጅምላ ጭፍጨፋ ወንጀል 5 ሺህ 160 ዓመት እስር ተፈረደበት

65
ህዳር 13/2011 ጓቲማላዊው የቀድሞ ወታደር በሀገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት በተፈጸመ ጭፍጨፋ እጁ አለበት በሚል ከ5 ሺህ 160 ዓመት እስር ተፈረደበት፡፡ በፈረንጆቹ 1982 ጓቲማላ ውስጥ ዶስ ኤሬስ በተባለች ሀገር በተፈጸመ ጭፍጨፋ ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን በ36 ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነት አሳዛኙ አጋጣሚ ነው ተብሏል። የቀድሞው ወታደር ሳንቶስ ሎፔዝ በአሜሪካ ስልጠና የተሰጣቸው የጓቲማላ ካይበለስ ሃይሎች አባል  እንደነበር ተገልጿል። ሎፔዝ በመንደሯ ከሞቱት ሰዎች መካከል በ171ዱ በእያንዳንዳቸው 30 ዓመት እስራት የተቀጣ ሲሆን በህይወት የተረፈች ሴት ልጅ እንድትገደል በነበረው ሚና ተጨማሪ 30 ዓመት ተቀጥቷል። በጓቲማላ ህግ መሰረት ማንኛው ግለሰብ በእስር ከተቀጣ ከፍተኛው ቅጣት 50 ዓመት ነው። ከፈረንጆቹ 1960-1996 በቆየው የ36 ዓመታት የጓቲማላ የእርስ በእርስ ጦርነት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሰላማዊ የማያን ማህበረሰብ ናቸው። ምንጭ፦ቢቢሲ  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም