የዲሞክራሲ ተቋማት በገለልተኛ አካለት እንዲመሩ የሚደረገው ጥረት የሚደነቅ ነው - የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት

96
አዲስ አበባ ህዳር 13/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየሰጡት ያለው ሹመት ከተለመደው አሰራር ወጣ ያለና የሰፊውን ህዝብ ፍላጎት የተከተለ ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ተናገሩ። የምክር ቤቱ አባላት ይህን የተናገሩት ዛሬ ባካሄዱት መደበኛ ስብሰባ ወይዘሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ካፀደቁ  በኋላ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በሰጡት አስተያየት ነው። ዛሬ የተሾሙትን ወይዘሪት ብርቱካንን ጨምሮ ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ በተለያየ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት ላይ የተሰየሙት ግለሰቦች በገዢው ፓርቲ የቆየ አሰራር ያልተለመደ፤ ሆኖም ግን በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍና አድናቆትን ያተረፈ ነው። ምክር ቤቱ ከሁለት ሳምንታት በፊት በተለይ ለፍትህ በመሟገት በስፋት የሚታወቁትን ወይዘሮ መአዛ አሸናፊን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አድርጎ መሾሙ ይታወሳል። ተሿሚዎቹ በትምህርታቸውም ሆነ በሥራ ልምዳቸው የላቁ፤ ለአገራዊ አንድነት፣ ፍትህና እኩልነት በፅኑ የሚታገሉ በመሆናቸው አገሪቱን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የተጀመረውን ዘርፈ በዙ ጥረት ለማሳካት ከፍተኛ አቅም  እንዳላቸው ነው የምክር ቤቱ አባላት የገለፁት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዲሞክራሲ ተቋማት በገለልተኛ አካላት እንዲመሩ የሚያደርጉት ጥረት የሚደነቅ እንደሆነ  የምክር ቤቱ አባላት አስረድተዋል፡፡ ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ረዳት ፕሮፌሰር አያሌው ዘለቀ እንዳሉት  መንግስታችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህዝብን የልብ ትርታ  በማድመጥ  ገለልተኛ በሆኑ ሰዎች  እንዲመሩ መደረጉ  አግባብ ነው ብለዋል፡፡ ወይዘሮ ገነት ኦንኬ  በበኩላቸወው በአቋማቸው ጠንካራ የሆኑትን ሰዎች በተለይም ሴቶችን፣  ወደ ሀላፊነት  በጠቅላይ ሚኒስትሩ ማምጣቱ  መልካም አጋጣሚ ነው ሲሉ ዛሬም የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ወይዘሪት በርቱካን ሚደቅሳም መሾማቸው ተገቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡  ተሿሚዎቹ በቀጣይ ህዝቡን የሚያረካና ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ስራ እንደሚሰሩ ያለቸውን እምነት የገለጹት አስተያየት ሰጪዎቹ የተሻለ ነገር እንደሚጠብቁም ተናግረዋል።  የምክር ቤቱ ድጋፍና ቁጥጥርም እንደማይለያቸው በመግለጽ።  ረዳት ፕሮፌሰር አያሌው ዘለቀ'' በተለይ በሳቸው የሚቋቋመው ቦርድና የሚመረጡ አባላት ለፍትህ መረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ” ምርጫን ከበፊቱ በተለየ መልኩ አዲስቷን ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የሚያረግግጥ ተቋም እንደሚፈጥሩ እምነታቸው መሆኑን የተናሩት  ወይዘሮ ገነት ኦንኬ ናቸው ፡፡ የምርጫ ቦርድ ገለልተኝነት ጋር በተያያዘ በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በገዢው ፓርቲ መካከል የቆየ ውዝግብ አለ። የዛሬው የወይዘሪው ብርቱኳን ሚደቅሳ የቦርዱ ሰብሳቢነት ሹመት ይህንን አለመግባባት በመፍታት ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው አስተያየት ሰጪዎች ይገልፃሉ።                      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም