የሐረር ከተማ የውሃ አቅርቦት ችግር አልተፈታም

65
 አዲስ አበባ  ህዳር 11/2011 ጥንታዊቷ የሐረሪ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ምንጯ የሆነው ሐረማያ ሐይቅ ከነጠፈ በኋላ ከውሃ አቅርቦት ችግር ልትላቀቅ አለመቻሏን ነዋሪዎቿ ለኢዜአ ገልጸዋል። ከሳምንታት በፊትም ሐረር የከፋ የውሃ ጥም አጋጥሟት 'ድረሱልኝ' ማለቷ አይዘነጋም። ኢዜአ ከሰሞኑ በከተማዋ ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ከሰሞኑ ቢሻሻልም ችግሩ በዘላቂነት እንዳልተቀረፈላቸው ይናገራሉ። የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በበኩሉ ችግሩን ለመፍታት እየጣረ እንደሆነ ገልጿል። እንደነዋሪዎቹ ገለጻ፤ ውሃ የሚያገኙት ከአንድ ወር እስከ ስድስት ወር እየቆዩ በመሆኑ ለከፍተኛ የኑሮ ጫና እየተጋለጡ ነው። ከአስተያየት ሰጭወቹ መካከል  ወይዘሮ እታለማው ተሾመ  ውሃ ተቋርጦ እስከ  ወር ፣ በሁለት ወር፣  አንዳንዱም ቦታ ደግሞ   እስከ ስደስት ወር  እንደሚቆይ አመላክተው  ችግሩ  አሳሳቢ መሆኑን  ተናግረዋል፡፡ አቶ ደመቀ የታየው "አልጋ ሁሉ አንሶላ ለማጽዳት ውሃ የለም። በየመንደሩ አንድ ጣሳ ውሃ ለማግኘት ህዝቡ እንደ እግዚአብሔር ውሃ እየለመነ ያለው።” የውሃ አቅርቦቱ  ለሁለት ወር ያህል ተቋርጦ  እንደነበር  አስታውሰው  አንድ ጄሪካን ውሃ እስከ 20 ብር ድረስ  መግዛታቸውን ያመላከቱት ደግሞ  አቶ ኢበሳ ሲራጅ  ናቸው፡  አሁን በአንጻንራዊ  መሻሻሉን  አመላክተው  በሳምንትና  በሁለት  ሳምንት  እንደሚመጣ ጠቁመዋል፡፡ የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የቴክኒክና ኦፕሬሽን የስራ ሂደት ኃላፊ አዲል በከሪ መሃመድ ሐረር ከድሬዳዋ፣ ኤረርና ሐረማያ አፋባቴ ከተሰኙ ስፍራዎች የከርሰ ምድር ውሃ እንደምታገኝ ጠቁመው ከድሬዳዋ አካባቢ ከሚመጣው በስተቀር የኤረርና ሐረማያ አፋባቴ የከርምደር ውሃ ምንጮች ለማሟያነት እንጂ የከተማዋን ህዝብ ውሃ ፍላጎት የሚያሟሉ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። ከዚህ በፊት የሚያጋጥመው የውሃ እጥረት ድሬዳዋ አካባቢ የሚገኘው የውሃ ጉደጓድ መጠን የመቀነስና የኤሌክትሪክ መቆራረጥ እንደነበር ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እንደ አማራጭ የሚያገለግሉት በኤረርና ሐረማያ አፋባቴ አካባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች የካሳ ጥያቄዎች በማንሳት የውሃ መስመሩን አቋርጠውት እንደነበር አስታውሰዋል። ባለስልጣኑ ለአካበባው ማህበረሰብ የቦኖ የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እንዲያገኙ ስራዎች ቢሰሩም ከዋናው መስመር የመጠቀም አዝማሚያዎች ስላሉ ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። በሌ በኩል በድሬዳዋ ያሉ የውሃ ጉድጓዶችን ጥልቀት ከ150 ሜትር ወደ 500 ሜትር በማሳደግ፣ የኤሌክትሪክ ፖል የሌላቸውን በመትከል የውሃ ፍሰቱ እንዳይቋረጥ የማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም