ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ አገራት መሪዎችና ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተወያዩ

66
አዲስ አበባ ህዳር 9/2011 ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአፍሪካ አገራት መሪዎችንና ከፍተኛ ባለሰልጣናትን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዛሬ ያነጋገሩት  የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ስማኤል ኡመርጊሌን፤ የታንዛኒያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኦገስቲን ማሂጋን እና የኮሞሮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሶኤፍ ሞሃመድን እንደዚሁም የቀድሞ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ሄለን ጆንሰን ሰርሊፍን ነው። Image may contain: 2 people, people smiling, people standing, stripes and outdoor ፕሬዝዳንቷ ከመሪዎቹ እና ባለስልጣናቱ ጋር ኢትዮጵያ ከአገራቱ ጋር ያላት ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ኃብታዊና ማህበራዊ ግንኙነት መጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መክረዋል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በምትችልበት መንገድ ላይም እንዲሁ። Image may contain: 2 people, people standing and suit የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሸብር ጌትነት እንደገለፁት በአገራቱ መካከል ያሉ የልማት፣ የምጣኔ ኃብት፣ የዜጎች የተረጋጋና ሰላማዊ የኑሮ ሁኔታ ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ ትስስሩን ማጠናከር እንደሚገባ መሪዎቹ ተወያይተዋል። በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ በአፍሪካ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ያደረሰና ያጠናከረ መሆኑም ተወስቷል። የለውጥ ሂደቱ የአህጉሪቷን ልማት፣ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ እድገት የተሻለ እንዲሆን የሚያግዝ በመሆኑ በዚህ ረገድ የሁሉም ሚና ሊጠናከር እንደሚገባና የሚበረታታ እንደሆነም መግባባት ላይ ደርሰዋል ነው ያሉት ዳይሬክተሩ። በአገሪቱ እየተከናወነ ያለው ለውጥ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካና ለቀጠናው ምሳሌ የሚሆን በመሆኑ ይህንን ማጠናከር ላይም በጋራ ለመስራት በውይይቱ ላይ ተስማምተዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እያበረከተች ያለው አስተዋጽኦ በተለይም የሪፎርም ስራዎችን በፍጥነት መተግበሯን ተከትሎ በአፍሪካ ህብረት ውስጥም ይህ ሪፎርም እንዲቀጥል ማደረጉም በውይይቱ ላይ ተነስቷል። መሪዎቹ በበኩላቸው ፕሬዝዳንቷ የኢትዮጵያ ርእሰ ብሄር ሆነው መመረጣቸው በአፍሪካ የሴቶችን አመራር ብቃት ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያደርስ እንደሆነ በውይይታቸው አንስተው የእንኳን ደስ አልዎት መልእክት አስተላልፈውላቸዋል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም