ታንዛኒያ ውስጥ በእስር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በምህረት እንዲለቀቁ ተጠየቀ

94
አዲስ አበባ ህዳር 9/2011 ታንዛኒያ ውስጥ በእስር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በምህረት እንዲለቀቁ ኢትዮጵያ ጠየቀች። ወደደቡብ አፍሪካ ሲያመሩ በታንዛኒያ የተያዙ 224 ኢትዮጵያዊያን በአስር ላይ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ የዜጎቿን ደንነት መጠበቅ ቀዳሚ አጀንዳዋ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ አስታውቀዋል። ዶክተር ወርቅነህ ገበየህ ከአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ጎን ለጎን ከታንዛኒያ አቻቸው ዶክተር አውጉስቲን ማሂጋ ጋር በሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው ይህንን ያስታወቁት። በታንዛኒያ ታስረው የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን በምህረት ተለቀው ወደአገራቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ  ሁለቱ ሚኒስትሮች መክረዋል። መንግስት በታንዛኒያ ያሉትን የዜጎች ደህንነት ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ዶክተር ወረቅነህ መናገራቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የታንዛኒያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር አውጉስቲን ማሂጋ በበኩላቸው  ኢትዮጵያውያኑ የሚለቀቁበትንና ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር አገራቸው እንደምትሰራ ተናግረዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም