በአፋር ለ46 ሺህ ልጃገረዶች የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ሊሰጥ ነው

85
ሰመራ ህዳር 7/2011 በአፋር ክልል ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሞላቸው ለ46 ሺህ ልጃገረዶች የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ መከላከያ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ። ክትባቱ በክልሉ 32 ወረዳና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች ከህዳር 11 እስከ 20 ቀን 2011 ዓ.ም በትምህርት ቤቶችና በጤና ተቋማት እንደሚሰጥ ቢሮው ገልጿል። በቢሮው የበሽታ መከላከልና ጤና ማበልጸግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዋሴ ሰዲቅ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት በሽታው ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሴቶች ላይ በስፋት የሚከሰት በመሆኑ ክትባቱን መስጠት አስፈልጓል። "ቢሮው  መንግስታዊና መንግሰትዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባባር በአምስት ሆስፒታሎችና በሰባት ጤና ጣቢያዎች ነጻ የማህጸንና የጡት ጫፍ ካንሰር ምርመራ እየሰጠ ነው" ብለዋል ። የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በሽታን ለመከላከል ክትባት አማራጭ መፍትሄ በመሆኑ በዘመቻ መልክ መስጠት ማስፈለጉን ተናግረዋል ። ህብረተሰቡ ሴት ልጆቹን እንዲያስከትብ በሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል ።                              
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም