ዋልያዎቹ ከጋና ብሄራዊ ቡድን ጋር በመጪው እሁድ ለሚያደርጉት ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ዋጋ ይፋ ሆኗል

94
አዲስ አበባ ህዳር 7/2011 ዋልያዎቹ ከጋና ብሄራዊ ቡድን ጋር በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲያም ለሚያድርጉት ጨዋታ ፌዴሬሽኑ የስታዲየም መግቢያ ዋጋ ይፋ አድርጓል። በ2019 ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ እየተሳተፉ የሚገኙት ዋልያዎቹ በመጪው እሁድ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ከጋና ብሄራዊ ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ስታዴየም ይጫወታሉ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ይህንን ጨዋታ ለማየት ለሚገቡ ተመልካቾች የክቡር ትሪቡን የመግቢያ ዋጋ 300 ብር መሆኑን አስታውቋል። እንዲሁም ጥላ ፎቅ 150 ብር፣ ከማን አንሼ ባለ ወንበሩ 75 ብር፣ ከማን አንሼ ወንበር የሌለው 40 ብር፣ ካታንጋ 25 ብርና ሚስማር ተራና ዳፍ ትራክ ደግሞ 15 ብር መሆኑን አስታውቋል።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም