አቶ ኢሳያስ ጠበቃ ይቁምላቸው ወይስ በራሳቸው ይከራከሩ የሚለውን ለመወሰን ለነገ ቀጠሮ ተሰጠ

63
አዲስ አበባ  ህዳር 6/2011 አቶ ኢሳያስ ጠበቃ ይቁምላቸው ወይስ በራሳቸው ጠበቃ አቁመው ይከራከሩ የሚለውን ለመወሰን ፍርድ ለነገ ህዳር 7 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ። አቶ ኢሳያስ ዳኘው የስራ ሃላፊ በነበሩበት ወቅት በኢትዮ ቴሌኮም ለሚሰራቸው የፓወር ተከላ ስራዎች ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ካለጫረታ በመስጠት ወንጀልና ምንጩ ያልታወቀ ከፍተኛ የሀብት አካብተዋል በሚል ተጠርጥረው መያዛቸውን ይታወቃል። ተጠርጣሪው ጠበቃ ለማቆም አቅም እንደሌላቸው መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ለፍርድ ቤት ማቅረባቸው ይታወሳል። በመሆኑም ፖሊስ የሚያቀርበውን ማስረጃ በመመርመው ጠበቃ በመንግስት ይቁምላቸው ወይም በራሳቸው ይከራከሩ የሚለውን ለመወሰን ፍርድ ቤቱ ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም