ከሜቴክ ጋር በተያያዘ በሙስና የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

117
አዲስ አበባ ህዳር 6/2011 ከብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር በተያያዘ በሙስና የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ። የመጀመሪያ ተጠርጣሪ ፍጹም የሺጥላ፣ ሁለተኛ ተጠርጣሪ ቸርነት ጌታነህ እና ሶስተኛ ተጠርጣሪ ወይዘሮ ትዕግስት ታደሰ ናቸው ዛሬ ችሎት የቀረቡት። ተጠርጣሪዎች ከሌላ ካልተያዘ ግብረአበር ጋር በመሆን ከሜቴክ ጋር ያለአግባብ የጥቅም ትስስር ነበራቸው ተብሏል። የመጀመሪያ ተጠርጣሪ 'ፍጹም ኢንተርቴይንመንት' በሚል በመሰረቱት ድርጅት ያለአግባብ ስፖንሰር በማድረግና ያለ ጨረታ በመውሰድ ተጠርጥረዋል። ተጠርጣሪዎቹ ከሜቴክ ጋር በተያያዘ ከ957 ሺህ በላይ ለፕሮጀክት የተመደበ የህዝብ ሃብት በመመዝበርና በህገ-ወጥ ደላላነት ተጠርጥረዋል። ጠበቆች የዋስትና መብት ያስፈልጋል በሚል የተከራከሩ ሲሆን ችሎቱ ትዕዛዝ ለመስጠት ለህዳር 17 ቀን 2011 ዓም ቀጠሮ ሰጥቷል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም