የካፋ ዞን ምክር ቤት በቦንጋ የተገነባው ብሄራዊ የቡና ሙዚየም ሥራ እንዲጀምር ወሰነ

52
ሚዛን ህዳር 6/2011 የካፋ ዞን ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባዔ ቦንጋ ላይ የተገነባው ብሔራዊ የቡና ሙዚዬም ሥራ እንዲጀምር ወሰነ። የካፋ ዞን የክልልነት ጥያቄንም በምክር ቤቱ አባላት ጸድቋል። የዞኑ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ ግርማ ወልደ ሚካዔል ለኢዜአ እንደገለጹት ጉባዔው በዛሬው ወሎ በሁለት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አስተሏልፏል ። ጉባዔው ውሳኔ ካሳለፈባቸው አጀንዳዎች አንዱ በዞኑ ቦንጋ ከተማ ተገንብቶ ለአመታት ሥራ ያልጀመረው ሙዚዬም ወደ ሥራ እንዲገባ ወስኗል። "ከምሁራን የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር ሙዚዬሙ ወደ ሥራ እንዲገባ ውሳኔ ተላልፏል" ብለዋል ። የካፋ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ ለምክር ቤቱ ቀርቦ በአባላቱ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በሙሉ ድምጽ መፅደቁን ምክትል አፈ ጉባዔው ተናግረዋል። ጉባኤው ነገ የዞኑን የ2010 በጀት ዓመት የአስፈጻሚ አካላት የሥራ ክንውን በመገምገምና በቀጣይ ዕቅድ ላይ በመወያየት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ አመላክተዋል ። እንደ ምክትል አፈ ጉባኤው ገለጻ በተለያዩ ምክንያቶች ያልጸደቀውን የዞኑን የ2011 በጀትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሹመትም እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም