ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከትግራይ ምዕራባዊ ዞን ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው

64
ሁመራ ህዳር 6/2011 የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በክልሉ ምዕራባዊ ዞን ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ጀምረዋል። የዞኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ የሺ ታረቀ ለኢዜአ እንደገለጹት ዛሬ ከቀትር በኋላ የተጀመረው ውይይት በልማት ፣በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። በዞኑ ከሚገኙ አራት ወረዳዎች የተወጣጡት የህዝብ ተወካዮችም በውይይቱ ላይ እየተሳተፉ ሲሆን በዞኑ የሚታዩ ዋና ዋና የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ያሉበትን ደረጃ እንደሚገመግሙ ተናግረዋል። ምክትል ርዕሰ-መስተዳደሩ ከተወካዮቹ ጋር በሚያደርጉት ውይይት ላይም ላጋጠሙ ችግሮች የመፍትሔ ሃሳብ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም