የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የቱሪስቶች ፍሰት እየጨመረ መምጣቱን ተገለፀ

160
ጎንደር ህዳር 6/2011 የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የቱሪስቶች ፍሰት እየጨመረ መምጣቱን የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ለቱሪስቶች የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ ነዋሪዎችና ማህበራትም ከቱሪዝም ዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ የፓርኩ ከፍተኛ የቱሪዝም ባለሙያ አቶ አዛናው ከፍያለው ለኢዜአ እንደተናገሩት በዘንድሮ የመጀመሪያው ሩብ አመት 3 ሺህ 139 የውጪ ሀገር ቱሪስቶች ፓርኩን ጎብኝተዋል፡፡ ፓርኩን የጎበኙት የውጪ ሀገር ቱሪስቶች ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነጻጸርም በአንድ ሺህ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡ የቱሪስቶች ቁጥር መጨመሩ የፓርኩንና የአካባቢውን ህብረተሰብ ገቢ እንዲጨምር አድርጎታል ያሉት ባለሙያው ለአብነትም በሩብ አመቱ ህብረተሰቡ ያገኘው 2 ሚሊዮን ብር ካለፈው አመት በግማሽ ሚሊዮን ብር ጭማሪ አሳይቷል፡፡ የፓርኩ ገቢ በሩብ አመቱ 663 ሺህ ብር መሆኑን የተናገሩት ባለሙያው  ካለፈው አመት በ200 ሺህ ብር ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡ ላለፉት 20 አመታት በአደጋ ቅርስ መዝገብ ውስጥ የቆየው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ  ባለፈው አመት በዩኔስኮ ውሳኔ ከአደጋ ቅርስ መዝገብ እንዲወጣ መደረጉ ለፓርኩ የቱሪስቶች ቁጥር መጨመር ተጠቃሽ ምክንያት ሆኖአል፡፡ የአካባቢው ሰላም አስተማማኝ እየሆነ መምጣቱና በውጭ ሀገር ፓርኩን ለማስተዋወቅ የተደረጉ የተቀናጁ ጥረቶች ለቱሪስቶች ፍሰት መጨመር አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ በፓርኩ ክልል ለቱሪስቶች በቅሎ በማከራየት ጓዝ በመጫንና መንገድ በመምራት አገልግሎት የሚሰጠው የኢኮ ቱሪዝም ማህበር ስራ አስኪያጅ ቄስ ሞገስ አየነው  ባለፉት ሶስት ወራት ማህበሩ 2 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡ ማህበሩ 7 ሺህ አባላት እንዳሉት የሚናገሩት ስራ አስኪያጁ አንድ የማህበሩ አባል ተረኛ ሆኖ ሲመደብ ለቱሪስቶች በቅሎ በማከራየትና ጓዝ በመጫን በቀን 400 ብር ገቢ እንደሚያገኝ ገልጸዋል፡፡ በፓርኩ ክልል ከእስካሁት ስራ በተጨማሪ ቱሪስቶችን በማጀብ ስራ የተሰማሩት አቶ ማረው ተረፈ "በወር አምስት ቀን ተራ እየገባሁ ቱሪስቶችን በማጀብ በየወሩ 2 ሺህ ብር ገቢ እያገኘሁ ነው" ብለዋል፡፡ ህብረተሰቡ ከቱሪዝም ዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን መንግስት ያመቻቸው ስምሪት "ፓርኩን በባለቤትነት እንድንጠብቅና እንድንከባከብ ምቹ ሁኔታ ፈጥሮልናል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1978 በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በአለም የተፈጥሮ ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡ ፓርኩ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙትን ዋልያ፣ ቀይ ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮ ጨምሮ የብርቅዬ የዱር እንስሳትና አዕዋፋት መገኛ ስፍራ መሆኑ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም